ኢስላም የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት
ይህንን ትምህርት ወደ ሚከተለው ቋንቋ ተቶርግሟል
- Русский - Russian
- العربية - Arabic
- ไทย - Thai
- অসমীয়া - Assamese
- Hausa - Hausa
- ગુજરાતી - Unnamed
- English - English
- Wikang Tagalog - Tagalog
- Tiếng Việt - Vietnamese
- සිංහල - Sinhala
- বাংলা - Bengali
- Кыргызча - Кyrgyz
- español - Spanish
- italiano - Italian
- فارسی دری - Unnamed
- azərbaycanca - Azerbaijani
- Mõõré - Mõõré
- тоҷикӣ - Tajik
- português - Portuguese
- svenska - Swedish
- नेपाली - Nepali
- čeština - Czech
- български - Bulgarian
- Deutsch - German
- 中文 - Chinese
- Bahasa Indonesia - Indonesian
- magyar - Hungarian
- Türkçe - Turkish
- فارسی - Persian
- Kurdî - Kurdish
- bosanski - Bosnian
- bamanankan - Bambara
- हिन्दी - Hindi
- Nederlands - Dutch
- മലയാളം - Malayalam
- پښتو - Pashto
- ქართული - Georgian
- Српски - Serbian
- Wollof - Wolof
- Kinyarwanda - Kinyarwanda
- polski - Polish
- Malagasy - Malagasy
- Lingala - Unnamed
- اردو - Urdu
- ئۇيغۇرچە - Uyghur
- română - Romanian
- Ўзбек - Uzbek
- Bi zimanê Kurdî - Bi zimanê Kurdî
- Chichewa - Nyanja
- Mandinka - Mandinka
- Kiswahili - Swahili
- македонски - Macedonian
ምድቦች
Full Description
ኢስላም
የተፈጥሮ፣ የአመክንዮና የደስታ ሃይማኖት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ራስዎን ግን ጠይቀው ያውቃሉ?
ሰማያትና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ግዙፍ ፍጥረታት ማን ነው የፈጠራቸው? በውስጣቸ ይህን ፍፁም የሆነ ረቂቅ ስርዓት የዘረጋውስ ማን ነው?
ይህ ታላቅ አጽናፈ ዓለም በረቀቀ ስርዓት በሚቆጣጠረው በዚህ መርህ ስር እንዴት ለዚህ ሁሉ ዓመታት ወጥ እና የተረጋጋ ሊሆን ቻለ?
ይህ ፍጥረተ ዓለም ራሱን ፈጠረ? ወይስ ያላንዳች ነገር የሆነ ነገር ሆነ? ወይንስ እንዲሁ ባጋጣሚ ተከሰተ?
ማን ፈጠረክ?
ይህንኑ ረቂቅ ስርዓት በርስዎ አካልም ይሁን በሌላውም ህያው ስርዓተ አካላት ላይ የዘረጋው ማን ይሆን?
«ይህ ቤት ማንም ሳይሰራው እንዲሁ የመጣ ነው።» ቢባል፤ ወይም ደግሞ «ይህንን ቤት ህልውና የሰጠው ህልውና የሌለው ነገር ነው።» የሚልን አስተሳሰብ ማንም አይቀበለውም። ታዲያ አንዳንድ ሰዎች «ይህ ታላቁ ዓለም ያለ ፈጣሪ የተገኘ ነው።» ሲባሉ አምነው የሚቀበሉት ለምን ይሆን?! አዕምሮ ያለው ሰው «ይህ ረቂቅ የሆነው የዓለም ስርዓት እንዲሁ ባጋጣሚ የመጣ ነው።» ሲባል እንዴት ይቀበለዋል?!
ያለጥርጥር ይህንን ዓለም በውስጡ ያለውንም የፈጠረና የሚያስተናብረው ታላቅ አምላክ ሊኖር ግድ ነው። ያም ጥራት የተገባው የላቀው አምላካችን አሏህ ነው።
ጥራት የተገባው ጌታችን አላህ መልዕክተኞቹን ልኮ፤ መለኮታዊ መጻሕፍትም (መለኮታዊ ራዕዩን) አውርዶላቸዋል። የመጨረሻው መጽሐፍም አላህ በመጨረሻው መልዕክተኛው ላይ ያወረደው የተከበረው ቁርአን ነው። በመጻሕፍቱና በመልዕክተኞቹ በኩልም:
አላህ ራሱን አስተዋወቀን፤ እርሱ በኛ ላይ እኛም በርሱ ላይ ያለንን መብትም አሳወቀን።
እርሱም መላ ፍጥረታቱን የፈጠረና የማይሞት ሕያው ጌታ መሆኑን፤ ፍጥረታቱም በአሸናፊነቱ፣ በኃያልነቱና በአስተናባሪነቱ ስር መሆናቸውን አስገነዘበን።
ዕውቀት ከባህርያቶቹ መካከል መሆኑንና ዕውቀቱ ሁሉንም ነገር ያካበበ መሆኑን፤ እርሱ በሰማይም በምድርም ምንም ነገር የማይደበቅበት ሰሚም ተመልካችም መሆኑንም ገለፀልን።
ጌታችን አላህ ‐ ጥራት ይገባውና ‐ ሕያው እና ራሱን ቻይ የሆነ ነው፤ የፍጥረታቱን ህይወት እርሱ በብቸኝነት የሚያስገኝ ህያው እና የፍጥረታቱን ሁሉ ህይወት እርሱ በብቸኝነት የሚያቋቁም ራሱን ቻይ የሆነ ጌታ ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:﴿اللَّهُ لا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لا تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلا نَوْمٌ لَهُ مَا فِي السَّمَوَاتِ وَمَا فِي الأَرْضِ مَنْ ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلا يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِنْ عِلْمِهِ إِلَّا بِمَا شَاءَ وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ وَلا يَئُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ﴾ {አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም (አያውቁም)፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡}[ሱረቱል በቀራ: 255]
በምሉዕነት ባህርያት የሚገለፅ ጌታ መሆኑንም ነገረን። ታላቅነቱን፣ ኃያልነቱንና የባህርያቱን ምሉዕነት በሚያመላክት መልኩም የፍጥረታቱን ድንቅ ተዓምራት የሚያስተውል አዕምሮና መንፈስ ለገሰን። በውስጣችንም ፍፁም መሆኑንና በጉድለት የማይገለፅ መሆኑን የሚያመለክት ተፈጥሮ ተከለልን።
ጌታችን አላህ በዓለም ውስጥ አልያም ዓለም በእርሱ ውስጥ ሳይሆን እርሱ ከሰማያቱ በላይ መሆኑንም አሳወቀን።
ጥራት ይገባውና እርሱ እኛንም ፍጥረተ ዓለሙንም ሁሉ የፈጠረ በመሆኑ ለርሱ እጅ ልንሰጥ እንደሚገባን ነገረን።
ስለዚህ ፈጣሪ መገለጫ ባህርያቱ የታላቅነት መገለጫዎች ናቸው። በፈላጊነት አልያም በጉድለት ፈፅሞ አይገለፅም። አምላክ አይረሳ፣ አይተኛ፣ ምግብም አይመገብም፤ ሚስት አልያም ልጅ ሊኖረውም አይገባውም። ከፈጣሪ ታላቅነት ጋር የሚጋጭ ሀሳብ የያዘ ጥቅስ ሁሉ አላህ መልዕክተኞቹን ‐ ዓለይሂሙ ሰላም ‐ የላከበት ከሆነው መለኮታዊ ራዕይ አይደለም።
የላቀው አላህ በተከበረው ቁርአን እንዲህ ብሏል:﴿قُلۡ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ * {በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ *ٱللَّهُ ٱلصَّمَدُ * «አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ *لَمۡ یَلِدۡ وَلَمۡ یُولَدۡ * «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ *وَلَمۡ یَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدُۢ﴾ «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡»}[አል‐ኢኽላስ: 1‐4]
በአምላክ ህልውና እስካመኑ ድረስ… ለምን እንደተፈጠሩስ ራስዎን ጠይቀው ያውቃሉ? አላህ ምን ይሆን ከኛ የሚፈልገው? የህልውናችንስ ዓላማው ምን ይሆን?
አላህ ከፈጠረን በኋላ እንዲሁ በከንቱ ትቶን ይሆን? አላህ እነዚህን ሁሉ ፍጡራን ምንም አላማ ወይም ግብ ሳይኖረው ይሆን የፈጠራቸው?
በእውነቱ ታላቁ ፈጣሪ ጌታችን "አላህ" እኛኑ የፈጠረበትን አላማ ነግሮናል። ይኸውም እርሱን በብቸኝነት ማምለክ ነው። እና ከኛ የፈለገው ምንድን ነው! እርሱ ብቻውን ለአምልኮ የተገባ መሆኑንም ነግሮናል። በመልዕክተኞቹ ዓለይሂሙ ሰላም በኩልም እንዴት እንደምናመልከው? ትእዛዛቱን በመፈፀምና ክልከላዎቹን በመታቀብ እንዴት ወደርሱ እንደምንቃረብ? ውዴታውን እንዴት እንደምንጎናፀፍ? ቅጣቱንም እንዴት እንደምንጠነቀቅ? ገልፆልናል። ከሞት በኃላ ስላለው መመለሻችንንም ነግሮናል።
ይህች የዱኒያ ህይወት ፈተና ብቻ መሆኗን፤ ፍፁም ትክክለኛዋ ህይወት ከሞት በኃላ በመጨረሻው ዓለም እንደምትሆንም ነግሮናል።
የታዘዘውን በመታዘዝ የተከለከለውንም በመቆጠብ አላህን ያመለከ ሰውም በዚህ ዓለም መልካም ህይወትን በመጪው ዓለምም ዘውታሪ ፀጋ እንዳለው፤ አላህን ያመፀና በእርሱ የካደ ሰውም በዚህ አለም እድለቢስነት በመጪው ዓለምም ዘውታሪ ስቃይ እንዳለው ነግሮናል።
እያንዳንዱ በዝህችው ህይወት ለሰራው በጎም ይሁን መጥፎ ስራ ምንዳውን ሳያገኝ እንደማይቀርም እኛ እናውቃለን። ግፈኞችም ቅጣታቸውን በጎ ሰሪዎችም መልካም ምንዳቸውን ሳያገኙ ሊቀሩ?!
ጌታችን አላህ ውዴታውን የመጎናፀፍና ከቅጣቱ የመዳን ስኬትን ወደ እስልምና በመግባት ካልሆነ በቀር እውን እንደማይሆን በርግጥ ነግሮናል። ይኸውም (እስልምና) ለአሏህ ተገዢ ሆኖ ያለምንም ተጋሪ እርሱን በብቸኝነት ማምለክ፤ ለትእዛዛቱም በታዛዥነት ተጎታች መሆን፤ መመርያውንም በደስታ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ነው። ከእርሱ ውጪ የሆነን ሃይማኖትም እንደማይቀበል ነግሮናል። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:(وَمَن يَبۡتَغِ غَيۡرَ ٱلۡإِسۡلَٰمِ دِينا فَلَن يُقۡبَلَ مِنۡهُ وَهُوَ فِي ٱلۡأٓخِرَةِ مِنَ ٱلۡخَٰسِرِينَ) (ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡)[አሊ‐ዒምራን: 85]
ዛሬ አብዛኞቹ ሰዎች የሚያመልኩትን የተመለከተ እዚጋ ሰው ሲያመልክ፣ ሌላው ጣኦትን ሲያመልክ፣ ሌላኛው ኮኮብን ሲያመልክ ያገኛቸዋል። ጤነኛ የሆነ ሰው በመገለጫ ባህርያቱ ፍፁም የሆነውን የአለማቱን ጌታ ካልሆነ ሊያመልክ አይገባውም። እንደሱ ያለ ሰውን አልያም ከሱም በታች የሆነን ፍጡር እንዴት ያመልካል? የሰው ልጅ፣ ወይም ጣኦት፣ ወይም ዛፍ አልያም እንሰሳም ሊመለክ የሚገባው አይደለም።
ከእስልምና ውጪ ያሉ ሰዎች ሃይማኖት አድርገው የያዟቸው ሁሉ የሰው ስሪት የሆኑ ሃይማኖቶች በመሆናቸው፤ ወይም ደሞ መለኮታዊ የነበሩ ሃይማኖት እንኳ ቢሆኑ የሰው እጅ የተጫወተባቸው በመሆናቸው አላህ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም። ኢስላም ግን የማይለወጥና የማይተካ የዓለማቱ ጌታ የአላህ ሃይማኖት ነው። የዚህ ሃይማኖት መጽሐፉም የተከበረው ቁርኣን ነው። እርሱም ልክ አላህ ባወረደው ጊዜ እንደነበረው ሁኔታ የተጠበቀ ነው። እስከ ዛሬ ድረስም በመጨረሻው መልዕክተኛ ላይ በወረደበት መሰረታዊ ቋንቋው በሙስሊሞች እጅ ላይ ይገኛል።
አላህ በላካቸው መልዕክተኞች ማመን፤ ሁሉም ሰዎችና አላህም በተዓምራትና በምልክቶች ያበረታቸው እንደነበሩ፤ ያለምንም ተጋሪ እርሱን በብቸኝነት ወደ ማምለክ ጥሪ ሊያደርጉ ዘንድ የላካቸው እንደሆኑ ማመን ከእስልምና መሰረቶች መካከል ነው።ከመልዕክተኞች የመጨረሻው መልዕክተኛ አላህ ከእርሱ በፊት የተላኩትን መመርያዎች የሚሽር የመደምደሚያውን መመርያ መለኮታዊ መልዕክቱን አስይዞ የላካቸው የሆኑት የአላህ መልዕክተኛ ሙሐመድ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈን) ናቸው። በታላላቅ ተዓምራትም አጠንክሯቸዋል፤ ከነዚህም ታላቁ ተዓምር የአሏህ ቃል፤ የሰው ልጆች ከሚያውቋቸው ሁሉ እጅግ ታላቅ የሆነው መጽሐፍ፤ በይዘቱም፣ በቃላቱም፣ በአደራደሩም፣ በህግጋቱም ተአምራዊ የሆነው መጽሐፍ፤ በውስጡም በዱኒያም በአኺራም ደስታን ወደሚያጎናፅፈው ሐቅ መምራትን ያጠቃለለ የሆነው፤ በዐረብኛ ቋንቋ የተወረደው እጅግ የተከበረው ቁርኣን ነው።
ይኸው ቁርኣን ያለጥርጥር ‐ጥራት የተገባው‐ የአላህ ቃል መሆኑንና በፍፁም የሰው ስሪት ሊሆን እንደማይችል የሚያመለክቱ በርካታ ሳይንሳዊና አምክንዯዊ ማስረጃዎች ይገኛሉ።
በመላዕክቱ ማመን እና በመጨረሻው ቀን ማመን፤ በዕለተ ትንሳኤ ሰዎች እንደሰሩት ስራ አይነት ሊመነዳቸው ዘንድ ሰዎችን ከየመቃብራቸው እንደሚቀሰቅሳቸው ማመንም ከእስልምና መሰረቶች ናቸው። አማኝ ሆኖ ስራውም መልካም የሆነ ሰው ጀነት ውስጥ ዘላቂ ፀጋ አለለት፤ የካደና ስራው ክፉ የሆነ ደሞ እሳት ውስጥ ከባድ ቅጣት አለለት። በጎም ይሁን መጥፎ አላህ በጻፈው ቀደር ማመንም ከእስልምና መሰረቶች መካከል አንዱ ነው።
የእስልምና ሃይማኖት ህይወትን በሙሉ ያጠቃለለ፤ ተፈጥሮንና አዕምሮን የሚስማማ፤ ጤናማ ነፍስ የምትቀበለው፤ ፈጣሪ ለፍጡራኑ የደነገገው የህይወት መስመር ነው። ኢስላም ለሁሉም ሰዎች ዘርን ከዘር፣ ቀለም ከቀለም ሳይለይ በዱኒያም በአኺራም መልካምንና ደስተኝነትን የሚያስገኝላቸው ሃይማኖት ነው። ሰዎች በእስልምና እኩል ናቸው። በእስልምና አንድ ሰው ከሌላው የሚለየው በመልካም ስራው ብዛት ብቻ ነው።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:(مَنۡ عَمِلَ صَٰلِحا مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤۡمِن فَلَنُحۡيِيَنَّهُۥ حَيَوٰة طَيِّبَة وَلَنَجۡزِيَنَّهُمۡ أَجۡرَهُم بِأَحۡسَنِ مَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ) (ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡)[አን‐ነሕል: 97]
አላህን እንደ ጌታና እንደአምላክ፣ ኢስላምን እንደሃይማኖት፣ ሙሐመድን እንደመልዕክተኝነት አምኖ ተቀብሎ ወደ ኢስላም መግባት የሰው ልጅ አማራጭ የማያገኝበት ግዴታ መሆኑን፤ በዕለተ ትንሳኤም ሂሳብና ምንዳ መኖሩ፤ ትክክለኛ አማኝ ለሆነ ሰው ስኬትና መዳን እንዳለለት ከሀዲ ለሆነው ደሞ ግልፅ ክስረት እንዳለለት አላህ በቁርኣን እጅግ ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው።
የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:(... وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ يُدۡخِلۡهُ جَنَّٰت تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ وَذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ، (… አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዙ ሰዎች ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፡፡ ይህም ትልቅ ዕድል ነው፡፡وَمَن يَعۡصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَتَعَدَّ حُدُودَهُۥ يُدۡخِلۡهُ نَارًا خَٰلِدا فِيهَا وَلَهُۥ عَذَاب مُّهِين) አላህንና መልክተኛውንም የሚያምጽ ወሰኖቹንም የሚተላለፍ በውስጧ ዘውታሪ ሲኾን እሳትን ያገባዋል፡፡ ለርሱም አዋራጅ ቅጣት አለው፡፡)[ኒሳእ: 13‐14]
ወደ እስልምና ሃይማኖት መግባት የፈለገ ሰው ትርጉሟን አውቆና አምኖባት እንዲህ ማለት ነው የሚጠበቅበት: "አሽሃዱ አን ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሃዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" (ትርጉሟም: ከአሏህ በቀር በእውነት ሊመለክ የሚገባው አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ እንደሆኑ እንደሆኑ እመሰክራለሁ ማለት ነው።) በዚህም ሙስሊም ይሆናል። ቀጥሎ አላህ ግዴታ ያደረገበትን ለመተግበር የተቀሩትን የእስልም ድንጋጌዎች አንድ በአንድ ይማራል።
አላህ ከፈጠረን በኋላ እንዲሁ በከንቱ ትቶን ይሆን? አላህ እነዚህን ሁሉ ፍጡራን ምንም አላማ ወይም ግብ ሳይኖረው ይሆን የፈጠራቸው?